ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ወደ መኖሪያቸው ካማሺ ዞን እንዲመለሱ የተደረጉ የቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቃዮች ወደየ አካባቢያቸው ቢመለሱም በቂ ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገለፁ።

የክልሉ መንግሥት ተፈናቅለው ከነበሩ መሃከል አብዛኞቹ ወደ አካባቢያቸው መመለሳውን ገልፀው የሚቀሩት 26 ሺህ ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/
ትናንት ባወጣው የኢትዮጵያን ሁኔታ በቃኘው ሪፖርቱ በክልሉ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ወደ የአካባቢያቸው መመለሳቸውን ጠቁሞ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስቧል።
/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/