ኢትዮጵያውያን በበረዶ በተዋጠችው ባፋሎ

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ የደረሰው ኃይለኛ ቅዝቃዜ ያስከተለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ የሰዎችን ህይወት ሲያጠፋ መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስተጓጉሏል። ይህ የበረዶ ማዕበል በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ካደረሰባቸው ስፍራዎች ደግሞ አንዱ ምዕራባዊው የኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የባፋሎ ከተማ ነው። በዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሳለፉት አነጋግረናቸዋል።