ዓቃቤ ሕግ በመስከረም አበራ ላይ ክስ እንዲመሰርት ሰባት ቀናት ብቻ ተፈቀደለት

Your browser doesn’t support HTML5

ዓቃቤ ሕግ በመስከረም አበራ ላይ ክስ እንዲመሰርት ሰባት ቀናት ብቻ ተፈቀደለት

ዓቃቤ ሕግ በእስር ላይ የምትገኘው “ኢትዮ ንቃት" የተባለው የዩቲዩብ ሚድያ አዘጋጅ በሆነችው መስከረም አበራ ላይ በሰባት ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃዋ ገለፁ።

ለ17 ቀናት ያህል በእስር ላይ የምትገኘው ኢትዮ ንቃት የተሰኘ የዩቲዩብ ሚዲያ አዘጋጅ መስከረም አበራ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ስትቀርብ የትናንቱ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የመስከረም አበራ የግል ጠበቃ ሰለሞን ገዛህኝ ትላንት "ምርመራየን አጠናቅቂያለሁ" ያለው ፖሊስ ግለሰቧን በተለያዩ ወንጀሎች መጠርጠሩን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ዐቃቤ ሕግ ለክስ መመስረቻ የ15 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት መጠየቁን ገልፀው ነገር ግን ይህንን መቃወማቸውንም ጠበቃው አክለው ተናግረዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ለክስ መመስረቻ የጠየቀውን የ15 ቀናት ጊዜ ውድቅ በማድረግ በሰባት ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ በመስጠት ለታኅሣስ 27/2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል

ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ ) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ፖሊስ መስከረምን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ጥሪ አቅርቧል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/