የአፍሪካ ኅብረት ቡድን በጥቂት ቀናት ውስጥ መቀሌ እንደሚገባ ተገለፀ
Your browser doesn’t support HTML5
የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት የሚገመግመውና የሚከታተለው የአፍሪካ ኅብረት ቡድን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መቀሌ እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎች ቡድን ጠቆመ። የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ትላንትናና ዛሬ ለሁለት ቀናት በናይሮቢ ያደረጉትን ሁለተኛ ዙር ውይይት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የአደራዳሪ ቡድኑ አባል የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ቡድኑ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ወደ መቀሌ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡