በባህር ዳር የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች እጥረት ገጥሟል

Your browser doesn’t support HTML5

በባህር ዳር የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች እጥረት ገጥሟል

በምልክት ቋንቋ የሠለጠኑ አስተርጓሚዎች በበቂ ሁኔታ ባለመኖራቸው የማኅበራዊ አገልግሎት ለማግኘት መቸገራቸውን መስማት የተሳናቸው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ ።

በማኅበር የተደራጁት መስማት የተሳናቸው ነዋሪዎች ወደ ፍትኅ፣ የህክምናና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋማት ሲሄዱ አስተርጓሚ በማጣት መቸገራቸውን በመግለጽ መንግሥት በየአገልግሎት ሰጭ ተቋማቱ አስተርጓሚ እንዲመድብ ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን የአካል ጉዳተኞችን በተለይ መስማት የተሳናቸውን ተጠቃሚ የሚያደርገው መመሪያ ክፍተት ያለበት መሆኑንና ህጉ እንዲሻሻል እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም በአሥር ተቋማት ውስጥ የምልክት ቋንቋ ባለሙያዋችን በብዛት እያሠለጠነ እንደሆነ አስረድቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።