አሜሪካ ውስጥ በመሳሪያ የሚፈፀሙ ጥቃቶችና የወላጆች ጭንቀት

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካ ውስጥ በመሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና የወላጆች ጭንቀት

የትምህርት ሳምንት ወይም 'Education Week' ተብሎ በሚጠራው የአሜሪካ ትምሕርት ቤቶችን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችና ዜናዎች የሚቀርቡበት ድረ ገፅ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በዚህ እየተገባደደ ባለው እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር 2022 ዓም በሀገሪቱ በትምህርት ቤቶች ውስጥ 46 የመሣሪያ ጥቃቶች ተፈጽመዋል።

በጥቃቶቹ ብዙ ህይወት ጠፍቷል። ብዙዎች ቆስለዋል። የደረሱትን ዘግናኝ ጥቃቶች ተከትሎ ታዲያ የመሳሪያ ባለቤትነት መብትን እና የትምህርት ቤቶች ደህንነትን በሚመለከት ክርክር እንደገና ተጧጡፎ ቀጥሏል።

የቪኦኤዋ ሊዛ ቮራ ቨርጂኒያ ውስጥ የሚኖሩ የተማሪዎች ወላጆችን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግራለች። "በትምህርት ቤቶች ውስጥ በመሳሪያ የሚፈጸም ጥቃት ይቆማል ብለን አናስብም። በመሆኑም ስለልጆቻችን ደህንነት እንፈራለን" ብለዋል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/