ትረምፕ በምክር ቤት ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋራ በተያያዘ አራት የወንጀል ክሶች እንዲቀርቡባቸው ተጠየቀ
Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ የቀድሞ ፕሬዚደንት በወንጀል እንዲከሰሱ ጠየቀ።
እንደ አውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ጥር 6 /2021 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚመረምረው ኮሚቴ ፤ የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ አመጹን ያካሄዱትን መርዳትን ጨምሮ አራት የወንጀል ክሶች እንዲመሰረቱባቸው ጠይቋል። ዘገባውን ያጠናቀረችው የቪኦኤ ምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን ናት።