ቲቦር ናዥ ለአሜሪካ ድምፅ የአድናቆት መልዕክት አስተላለፉ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል የዩናይትስ ስቴትስ የቀድሞ አፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናዥ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ሰኔ 2012 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ

የዩናይትስ ስቴትስ የቀድሞ አፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናዥ የአሜሪካ ድምፅ ትናንት ሰኞና ዛሬ በሁለት ክፍሎች ላስተላለፈው ውይይት በትዊተር መልዕክታቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

“የአሜሪካ ድምፅ ከተለያዩ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የወጡ፣ ወደፊት ለመራመድ ምን ያስፈልጋል በሚል ሃሳብ ላይ ያሏቸውን ልዩነቶች አበርትተው ሊከራከሩ የሚችሉ ግን አብረው ተቀምጠው የተነጋገሩ ትውልደ-ትዮጵያን "ኢትዮጵያ- የሰላም መንገዶች" ላይ በአንድ የውይይት መድረክ ላይ ተሰብስበው በግልፅነት እንዲወያዩ በማስቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ረዳት ሚኒስትር ናዥ በዛሬ ትዊታቸው።