ቆይታ ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ እና "ኮሚሽነር" ጌራወርቅ ከተማ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ካገለገሉ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች መካከል አንዷ ጌራ ወርቅ ከተማ ናት ። በአሁኑ ሰዓት በጨዋታ ታዛቢነት (ኮሚሽነርነት ) እያገለገለች ያለችው ጌራ ወርቅ ፣ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች እንዲበራከቱ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ትናገራለች ። የዓለም ዋንጫን አስታከን በእንግድነት የጋበዝናት ጌራወርቅ ፣ ስለሙያዊ ጉዞዋ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳቦቿን ታጋራናለች ።