27 ኢትዮጵያውያን አስክሬን ከሉሳካ ወጣ ብሎ በሚገኝ እርሻ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

27 ኢትዮጵያውያን አስክሬን ከሉሳካ ወጣ ብሎ በሚገኝ እርሻ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ

27 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች አስክሬን ዛምቢያ ውስጥ ከዋና ከተማዋ ሉሳካ ወጣ ብሎ በሚገኝ ንጌዌሬሬ የእርሻ ቦታ ትናንት እሁድ ታኅሣሥ 2 / 2015 ዓ.ም ተጥሎ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

አስከሬናቸው የተገኘው ኢትዮጵያውያን የሞቱት በረሃብና በድካም ምክንያት ነው ተብሎ እንደተጠርጠረ የዛምቢያ ባለሥልጣናት ገልፀዋል። ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች በደረሰው ጥቆማ መሰረት አስክሬኖቹን አግኝቶ ባደረገው የመጀመሪያ ምርመራ ባልታወቁ ሰዎች መንገድ ዳር የተጣሉት ሁሉም በ20ና በ 38 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የነበሩ ወንዶች መሆናቸውን አመልክቷል።

አስከሬኖቹ በተገኙበት ወቅት አንድ ሰው ብቻ በህይወት የተገኘ ሲሆን ህክምና እንዲደረግለት በጥድፊያ ሉሳካ ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዱ ተገልጿል።

የሟቾቹ አስከሬኖችም ማንነታቸውን ለመለየትና በምን ምክንያት እንደሞቱ ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲካሄድ ወደአስከሬን ማሳረፊያና መመርመሪያ ስፍራ መወሰዳቸውን የፖሊስ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

አስክሬኑ ሲሰበሰብ ቦታው ላይ ሆነው ማየታቸውንና ገልፀው ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ አንንዲት ኢትዮጵያዊት፤ኢትዮጵያውያኑ ለእንዲህ ያለ ችግር የሚጋለጡት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንወስዳችኋለን በሚሉ በሚል በሕገወጥ ደላሎች በመታለል ነው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር ቃል አቀባይ መለስ አለም በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሉ ሉሳካ አቅራቢያ ሕይወታቸው ስላለፈ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መንግሥታቸው መረጃ እንደደረሰው ገልፀው፤ ጉዳዩ የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ተገልጿል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/