አክሱምና ዐድዋ በጥቂት ቀናት ውስጥ የስልክ አገልግሎት ይጀምራል ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል በአክሱምና ዓድዋ ከተሞች በጥቂት ቀናት ውስጥ የስልክ አገልግሎት እንደሚጀመር ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡ ባለፈው ሳምንት በሙከራ ላይ የነበረው የሽረ ከተማ የስልክ ግንኙነትም በይፋ መጀመሩን የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡