ምዕራባውያን የዩክሬኑ የሩሲያ ጦርነት “አረመኔያዊ ነው” አሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ምዕራባውያኑ ኃያላን አገሮች ሩሲያ በጎረቤቷ ዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት “አረመኔያዊ” ሲሉ ፈርጅውታል። ክሬምሊን እጅግ በቀዘቀዘው ክረምት ውስጥ ወሳኝ በሆኑ የዩክሬን መሠረተ ልማቶች ላይ የምታካሂደውን ጥቃት መጨመሯን ተከትሎም ምዕራባውያኑ ምላሹን ሩሲያ ወደ ውጭ በምትልከው ነዳጅ ላይ ለማሳረፍ እየሞከሩ ነው። ሞስኮ ግን ሙከራዎቹን አልተቀበለችውም፡፡