ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር ሦስት ፓርቲዎች ጠየቁ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት ስር እንዲተዳደርና አካባቢውንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲቆጣጠረው ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ፡፡እናት፣ ኢህአፓና መኢአድ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣መንግሥት ቁጥራቸው ለበዛ ሰላማዊ ሰዎች ህልፈትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑት ኃይሎችን ለሕግ እንዲያቀርብና በአካባቢው እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት ለሕዝብ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ አሳስበዋል።