ኢትዮጵያዊ ባህል እና ማንነት የሚገነባ ተቋም
Your browser doesn’t support HTML5
ከኢትዮጵያ ውጪ የተወለዱ ህፃናት ወላጆቻቸው የመጡበትን ቋንቋ፣ ባህል፣ እና ልማድ አውቀው እንዲያድጉ ለማገዝ ከአራት አመት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ግዛት የተቋቋመው አቦጊዳ የቋንቋ እና ባህል ተቋም፣ ህፃናት የአማርኛ ቋንቋን እንዲናገሩ እና እንዲያነቡ ብቻ ሳይሆን ከዛም ባለፈ ስነ-ፅሁፎችን፣ ግጥሞችን እና ስነ-ቃሎችን እንዲማሩ እያገዘ ይገኛል። ልጆች በስነምግባር ታንፀው እንዲያድጉም አብሮነትና መከባበርን የሚያንፀባርቁ ባህልና ታሪኮችንም ያስተምራል።