ለ"ቀይ ባህር አፋር" ስደተኞች ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ሰልፍ ተደረገ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ ለተጠለሉ "የቀይ ባህር አፋሮች " በቂ ትኩረት እና ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ሰልፍ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተደርጓል።በሰርዶ ፣ በርሃሌ እና አሳይታ አካባቢ ተጠልለው የነበሩ ስደተኞች በቀጠናው በነበረው ግጭት ምክንያት ለከፋ ሁኔታ መዳረጋቸውን የተናገሩት የሰልፉ ተሳታፊዎች ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ስደተኞች ወደ ሶስተኛ ሀገር የሚወሰዱበትን መንገድ እንዲያመቻች ከሰሞኑ ጠይቀዋል።