የአየር ንብረት ጉባኤ ተጠናቋል

Your browser doesn’t support HTML5

የተባበሩት መንግሥታት ያዘጋጀውና ቀደም ሲል ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀው በአየር ንብረት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ትናንት እሁድ ማለዳ ተጠናቋል።

“ለኪሳራ እና ለጉዳት” መርጃ የሚል መጠሪያ የተሰጠው እና የአየር ንብረት ለውጥ ላስከተላቸው ጉዳቶች የሚውል ገንዘብ መመደብ አለበት በሚለው ሐሳብ ላይ መስማማት ተችሏል።

ይህም እንደ ተንታኞች እይታ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ሕዝቦች ለመርዳት አንዳች ሁነኛ እርምጃ ተደርጎ ታይቷል።

ይሁንና በብራዚል ጎርፍ ባስከተለው ናዳ የደረሰውን የመሰለ መኖሪያ ቤቶችን የቀበረውን ዓይነት አደጋ ለመከላከል ከገንዘብ በላይ የሆነ እርምጃ ያስፈልጋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።