ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ድሮኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አደረሱ ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ድሮኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አደረሱ ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ ወረዳ መንዲ ከተማ ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም በሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

ዕለቱ የገበያ ቀን በመሆኑም ጥቃቱ ሲፈፀም በርካታ ሰዎች በቦታው እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የኦሮሞ ነፃነት ጦር ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ አቶ ኦዳ ተርቢ ጦራቸው መንዲ ከተማን መቆጣጠሩን ገልፀው የድሮን ጥቃቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንጂ በእነርሱ ላይ ጥቃት አላደረሰም ሲሉ አስተባብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከፌደራል መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። አንድ የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣን ሸኔ መንዲ ከተማን ተቆጣጥሮ ስለነበረ መንግሥት እርምጃ ሲወስድባቸዉ እንደነበረ ገልፀው በድሮን ጥቃቱ የሸኔ አባላትእንጂ ሰላማዊ ሰዎች እንዳልተጎዱ ተናግረዋል።/ዘገባውን የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ሆራ ነው።/