አማራ ክልል የሚገኙ የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ክልል ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

አማራ ክልል የሚገኙ የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ክልል ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የምዕራብ ጎጃም ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ማኅበረሰቡን ተቀላቅለው እንደሚገኙ ገልጾ ለእርዳታ አቅርቦቱ ቁጥራቸውን በማጣራት ላይ መሆኑን አመልክቷል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮምሽንም ተፈናቃዮቹ በቂ ድጋፍ አለማግኘታቸውን አስታውቋል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/