የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ

Your browser doesn’t support HTML5

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ

በፌዴራል መንግስትና በህወሃት መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስምምነቱ ተግባራዊነት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

“በአሸባሪነት ከተፈረጀ አካል ጋር እንዴት ድርድር ተፈጸመ?” በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ የኢትዮጵያ ሕግ ይህን እንደማይከለክል ገልጸው ዓለም አቀፍ ልምዶችን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተዋል።

የትግራይና የአማራ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡበትን ስፍራ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ “የፕሪቶሪያው ድርድር ይህን የሚመለከት አይደለም” በሚል መልሰዋል፡፡ ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ሕጋዊ እልባት እንደሚሰጠውም አብራርተዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እስካሁን ከህወሃት በኩል በቀጥታ የተሰጠ ምላሽና አስተያየት የለም፡፡