በአሜሪካው የአማካይ ዘመን ምርጫ መወሰኛው ምክር ቤት በዲሞክራቶች እጅ ይቆያል
Your browser doesn’t support HTML5
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአማካይ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች ሁለቱንም ምክር ቤቶች ይቆጣጠራሉ ተብሎ እንደተተነበየው ሳይሳካላቸው ቀርቷል። እስከአሁን ባለው የድምጽ ቆጠራ መሠረት ዲሞክራቶች በመወሰኛ ምክር ቤቱ ቢያንስ 50 መቀመጫዎች ይዘዋል። ሪፐብሊካኖች ደግሞ የተወካዮች ምክር ቤቱን አብላጫ መቀመጫ ወደመያዝ እያመሩ ናቸው። አሸናፊው ማን እንደሆን በውል ያልተለየባቸው ፉክክሮችም አሉ። /ዘገባው የአራሽ አራባሳዲ ነው። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/