በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት መቀጠሉን የገለፀው የትምህርት ሚኒስቴር ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ሌሎች የተለያዩ ጥረቶች እንደሚደረጉም የትምሀርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡
የመውጫ ፈተና መስጠት፣ ተመራቂዎች በሚቀጠሩበት ጊዜ ፍትሀዊ ውድድር እንዲያደርጉ ያግዛል፣ ተቀራራቢ ብቃት እንዲኖራቸውም ያስችላል ይላሉ ምሁራን፡፡
ሆኖም፣ እርምጃው የራሱ የሆኑ ችግሮች እንደሚኖሩት ምሁራኑ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡