የልብ ህሙማንን የምትረዳው የልብ ታማሚ የሕክምና ባለሞያ

Your browser doesn’t support HTML5

አክሊለ በቀለ የልብ ችግር እንዳለባት የታወቀው ገና የስድስት ወር ጨቅላ ህፃን እያለች ነበር፡፡ ዕድሜዋ ሁለት አመት ከስምንት ወር ሲደርስ የልብ ሕመሟ እየጠና በመምጣቱ የዛሬ 19 ዓመት በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል እገዛ በውጭ ሀገር የቀዶ ህክምና ተደረገላት፡፡ በዚህም ጤንነቷ ሊስተካከል ችሏል፡፡ አሁን የልብ ህሙማን ህፃናትን ለመርዳት በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ማገልገል ጀምራለች፡፡