ዚምባብዌ የምዕራባውያንን ማዕቀብ የሚቃወም ድጋፍ እያሰባሰበች ነው
Your browser doesn’t support HTML5
በመቶዎች የሚቆጠሩ የዚምባብዌ ዜጎች ለሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጠያቂ የሚያደርጉትን ምዕራባውያን የጣሉባቸውን ማዕቀቦች ተቃውመው የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። እነዚህ ከሀያ አመታት በላይ ያስቆጠሩ ማዕቀቦች የተጣሉት፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በስልጣን በነበሩት ወቅት አካሂደዋል ተብለው በተከሰሱበት የምርጫ ማጭበርበሮች እና የመብት ጥሰቶች ምክንያት ነው።አሜሪካ እና እንግሊዝ ግን ማዕቀቦቹ ዚምባብዌ አሁን ላለችበት ችግር መንስኤ አይደሉም የሚል አቋም ያራምዳሉ።