የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ኩረጃን ለመከላከል ትምህርት ሰጥቷል

Your browser doesn’t support HTML5

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ቅጥር ግቢ መሰጠቱ የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን ለመከላከል የሚያስችል ትምህርትና ልምድ እንዳገኘበት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የተቋሙ የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወርቅ እዝቅኤል ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በፈተናው ሂደት ከታዩት ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች ትልቅ ትምህርትና ልምድ አግኝተናል ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንዳንድ ወላጆችና ተማሪዎችም ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች በመሰጠቱ ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል።