በኢትዮጵያው ግጭት አሁናዊ ሁኔታዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት በሠላም መፍታት በሚቻልበት ጉዳይ አዲስ አበባ ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ፡፡

በሌላ ዜና፣ ጦርነቱ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አቅጣጫዎች ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉ የህወሓቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ስለጦርነቱ ምንም አይነት መግለጫም ይሁን ምላሽ ከመስጠት እንደተቆጠበ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ “አየርላንድ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ከሚጻረሩ ድርጊቶቿ ልትታቀብ ይገባል” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አሳሰበ፡፡

ይህ ካልሆነ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችንን አስፈላጊነት እናጤለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአየርላንድ መንግሥት በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

ለደብዳቤው እስካሁን ከአየርላንድ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]