በሊባኖስ በሚገኙ የቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃትን የተመለከተ ጥናት ይፋ ተደረገ

Your browser doesn’t support HTML5

በሊባኖስ በሚገኙ በቤት ሰራተኝነት በሚያገለግሉ ሴቶች ላይ ይፈጸማል የተባለን ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን የተመለከተ ጥናት ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል። አስር ወራትን የፈጀው ጥናት በሀገሪቱ የህግ ከለላ ያጡ ሰራተኞች እየደረሰባቸው ያለውን ጾታዊ ጥቃት ስፋት እና ለመፍትሄነት መተግበር ያለባቸውን እርምጃዎች አመላክቷል። ጥናቱን ከሊባኖስ አሜሪካ ዩኒቨርሰቲ ባልደረባ ጋር በትብብር ያደረገው "እኛ ለእኛ" የተባለው የስደት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ባንቺ ይመርን አነጋግረናል።