በቤኒሻንጉል ጉምዝ ሴቶች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ለማገዝ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የሴቶች ትምህርት ተሳትፎ አናሳ ከሆነባቸው አካባቢዎች አንዱ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሲሆን በተለይ ወደ ሁለተኛ ደረጃ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ ነው። ኩሶ ኢንተርናሽናል የተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም ታዲያ ይህንን ለመቀየር እና ሴቶች በትምህርታቸው ትልቅ ደረጃ እንዲደርሱ ለማድረግ ትልቅ ጥረት እያደረገ ሲሆን ከ700 በላይ ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች ህይወት መቀየር ምክንያት ሆኗል።