የድሬዳዋ የትግራይ ተወላጆች ከአስተዳደሩ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

Your browser doesn’t support HTML5

በድሬዳዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር ምክክር አደረጉ።

የአስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙ የትግራይ ተወላጆች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት፣ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አሁን አሉባቸው ስላሏቸው ችግሮች፣ እንዲሁም በድሬዳዋ ነዋሪነታችን እያጋጠሙን ነው፤ ባሏቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ጉዳዮች አንስተው ከአስተዳደሩ ጋር ተወያይተዋል።