ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያውያን ላይ ተጨማሪ እገዳ ጣለች

People gather in front of a large screen to celebrate the incorporation of regions of Ukraine into Russia, in Sevastopol, Crimea, Sept. 30, 2022. The signing of the treaties making the four regions part of Russia followed the completion of Kremlin-orchest

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን አራት የዩክሬን ግዛቶችን ገንጥለው ከጠቀለሉ በኋላ፣ የባይደን አስተዳዳር ፑቲንን በሚደግፉና፣ በሩሲያ ውስጥም ሆነ ውጭ በሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ትናንት አዲስ ማዕቀብ ጥሏል።

በአሜሪካ የሚገኝ ንብረትና ገንዘብ ላይ፣ እንዲሁም የቪዛ ማዕቀብ በመቶ በሚቆጠሩ የሩሲያ ድርጅቶች፣ የሃገሪቱ ባለስልጣናትና ቤተሰቦች ላይ ሲጣል፤ ለውጪ ገበያ በሚልኩት ምርት ላይም እገዳ መደረጉን የቪኦኤዋ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ከዋይት ሃውስ ዘግባለች።

ለሩሲያ መሳሪያ የሚያቀርቡና፣ አቅርቦቱን የሚያቀላጥፉ 14 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም በማዕቀቡ ተመተዋል። ይህም የሩሲያን ጦር መልሶ የማገገም ብቃት ይጎዳል ተብሏል።

አራት የዩክሬን ግዛቶች ወደ ሩሲያ በመጠቃለላቸው የፑቲን ደጋፊዎች ደስታቸውን ለመግልጽ ትናንት በቀዩ አደባባይ ተሰባስበው ታይተዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በጥድፊያ የተፈጸመውን ህዝበ ውሳኔ ዩክሬንና የምዕራቡ ዓለም ውድቅ አድርገውታል። ግዛቶቹ ወደ ሩሲያ መጠቃለላቸውን በማስመልከት በተደረገ የፊርማ ሥነ ስራት ላይ ፑቲን እንዳሉት፣ አንድ አምስተኛውን የዩክሬን ግዛት በሚያክሉት በአራቱ ክልሉች፤ ማለትም ሉሃንስክ፣ ዶነትስክ፣ ኬርሶን እና ዛፖሪዤዢያ የሚገኙ ሕዝቦች “እስከወዲያኛው ዜጎቻችን ሆነዋል” ብለዋል።