የትምህርት መረጃ ስርዓትን ለማዘመን ያለመ "ኢ-ስኩል" የተሰኘ አገልግሎት ተዋወቀ
Your browser doesn’t support HTML5
ግጭት እና ጦርነት በከረመባት ኢትዮጵያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከገጠማቸው ችግሮች መካከል አንዱ የትምህርትተቋማት ፣ መረጃ እና መዛግብት ውድመት እንደሆነ ሲነገር ተሰምቷል። እንዲህ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ብሎም የተለመደው የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት ለማዘመን ያለመ " ኢ-ስኩል" የተሰኘ ስርዓት ፣ ዋልያ ቴክኖሎጂስ በተባለ ተቋም በኩል ከሰሞኑ ተዋውቋል። ስለ "ኢ-ስኩል" ምነነት እና ፋይዳ እንዲያስረዱን የዋልያ ቴክኖሎጂ መስራች አቶ አንተነህ አስራትን ጋብዘናል ።