መጽሃፍትን ለትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ፣ ቆይታ ከታቲያና ክፍሌ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ታቲያና ክፍሌ ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች የስድስት የህጻናት መጽሃፍት ደራሲ እና በርከት ያሉ የህጻናት ሙዚቃዎች አዘጋጅ ናት። በተከታታይ ለአንባቢያን ባቀረበቻቸው መጽሃፍት ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ከባህላቸው ጋር እንዲተዋወቁ፣ የወላጆቻቸውን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲለምዱ በማገዝ ላይ ትገኛለች። ሀብታሙ ስዩም በቅርቡ በተደረገው "ቴስት ኦፍ አፍሪካ " ትርዒት ላይ ታቲያናን አግኝቶ ከስራወቿ ጋር የተገናኙ ጥቂት ጥያቄዎችን አቅርቦላታል።