ለችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያንን ለመደገፍ ያለመ ዝግጅት በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ

Your browser doesn’t support HTML5

ለችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያንን ለመደገፍ ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከሰሞኑ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄዷል። "ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ የተግባር ቡድን " የተባለ ተቋም ባስተባበረው በዚህ መድረክ ላይ ከገቢ ማሰባሰቢያ መሰናዶዎች በተጨማሪ ተጋባዥ እንግዶች ንግግር አድርገዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ሀገሪቱን ወደ ዳግም ግጭት በማስገባት ለሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ዳርጓታል ያሏቸውን የትግራይ ኃይሎች ወቅሰዋል ።የአሜሪካ ድምጽ ያናገራቸው በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የትግራይን ክልል መንግስት ወኪል በበኩላቸው መሰል ውንጀላዎችን አስተባብለዋል ።ሀብታሙ ስዩም ቀጣዩን ዘለግ ያለ ዘገባ አሰናድቷል ። ።