አጭር ቆይታ ከስነ-ጥበብ እና ፊልም ባለሙያው ተስፋዬ ወንድም አገኝ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ለኢትዮጵያ ፊልም ወዳጆች ተስፋዬ ወንድማገኝ የሚለው ስም አዲስ አይደለም ። ተስፋዬ "ስርየት"ን በመሰሉ ፊልሞች፣ "ጥቁር ሰው" ን በመሰሉ የሙዚቃ ቪዲዮች ላይ ልዩ ጥበብን በሚጠይቁ የስነ-ገጽ (ሜክ አፕ) እና የፊልም ገጽ መሰናዶ (አርት ዳይሬክቲንግ) አሻራውን የተወ ባለሙያ ነው።በአሁኑ ሰዓት ነዋሪነቱን በአሜሪካን ሀገር ያደረገው ተስፋዬ ከሰሞኑ ወጥ የስዕል ስራዎቹን ለዕይታ አቅርቧል። ከስራዎቹ ጋር የተገናኙ ጥቂት ጥያቄዎችን አቅርበንለታል ።