የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለቪኦኤ እንደገለፁት፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በመሰረተ ልማት ላይ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት አድርሷል፡፡
በጦርነቱ ውድመት ከደረሰባቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፍያ መሳሪያዎች እና የማከፋፈያ ጣቢያዎች በተጨማሪ በመሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈፅሟል ሲሉ አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡
አሁን ዳግም ያገረሸው ጦርነትም በመሰረተ ልማት ላይ ተመሳሳይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ጠቅሰው፣ ግጭቱ ቀደም ሲል ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ኃይል ለማቅረብ የሚደረግን ጥረት ያሰናክላል ብለዋል፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Your browser doesn’t support HTML5