በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ በህጻናት ላይ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የሕክምና ዕርዳታ ከተደረገላቸው ዜጎች መካከል ሦስት ህፃናት መሞታቸውን የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ከ800 በላይ ሰዎች በወረዳው በሚገኙ የጤና ተቋማት መታከማቸውንም ይፋ ተደርጓል።

በሌላ በኩል በወረዳው በተከሰተ ድርቅ ከ150 ሺህ በላይ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል።