ምዕራብ ትግራይ ወይም ወልቃይት ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የቆየውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው የሰላም ንግግር ወቅት አጨቃጫቂ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል የአሜሪካ ድምፁ ሄንሪ ዊልክንስ ከአዲ-ረመፅ ባጠናቀረው ዘገባ አመልክቷል።
ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር የወገኑ ኃይሎች አሁን ሥፍራውን እንደሚቆጣጠሩ ሪፖርቱ ጠቁሞ “የትግራይ ኃይሎች ግን የሰላም ንግግሩን ወደፊት ለማስኬድ አካባቢው ወደ ትግራይ መመለስ አለበት እያሉ ነው” ብሏል።
ሄንሪ ዊልኪንስ ባለፈው ግንቦት ለሌሎች እንደልብ የማይገኝ ፍቃድ አግኝቶ አካባቢውን ቃኝቶ ነበር። በዚህ ሪፖርት ደግሞ ሁለቱም ወገኖች አካባቢው ወዴት ይካለላል በሚለው ጉዳይ ላይ ለምን ጠንካራ አቋም እንደያዙ ይመለከታል።