ስለ "ቡሄ" በዓል እና ዝማሬዎች ፣ ቆይታ ከመምህር አቤል ተስፋዬ ጋር
Your browser doesn’t support HTML5
ህጻናት እና ወጣቶች የክረምቱን መገባደድ የአዲሱን ዘመን መቃረብ በጭፈራ እና በዝማሬ ከሚያበስሩባቸው በዓላት መካከል አንዱ "ቡሄ" ነው። ይህ ባህላዊ እና ኃይማኖታዊ መሰረት ያለው በዓል ከእነወዘናው ዓመታትን ይሻገር ዘንድ ለወጣቶች ስልጠና እና ድጋፍ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ መምህር አቤል ተስፋዬ ናቸው ። ዘማሪ፣ የበገና አደራደር እና ክራር ባህላዊ መሳሪያ አስተማሪ የሆኑት መምህር አቤል ስለ ቡሄ በዓል ፣ዝማሬዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን ያቀብሉናል።