"ትምህርት ቤቶች የፈተና ማዘጋጃ ብቻ ሆነዋል"-የተማሪ ቤት መስራች ሀብታሙ አሰፋ

Your browser doesn’t support HTML5

ተማሪ ቤት ተማሪዎች ስለ ሚማሩት ነገር በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው በማስቻል ፣ የኢትዮጵያን ትምህርት አሰጣጥ ለማዘመን ያለመ ተቋም ነው። ተቋሙ ከፊት ለፊት ጥናት አገልግሎት በተጨማሪ ፣ በዲጂታል የቪዲዮ እና የጽሁፍ ማስተማሪዎች ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዕውቀትን ያዳርሳል። ስለ ተማሪ ቤት የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም የአገልግሎቱን መስራች ሀብታሙ አሰፋን አነጋግሯል ።