ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሕብረት ውጪ አደራዳሪ እንደማትቀበል አስታወቀች

Your browser doesn’t support HTML5

ከትግራይ ክልል መንግሥት ወይም ከህወሓት ጋር ይካሄዳል ለተባለው ድርድር ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ አደራዳሪ እንደማይቀበል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከሕብረቱ በተጨማሪ የሚደረግ የአደራዳሪነት ጥረት በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል።

በሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ላይ እምነት እንደሌለው የገለጸው ሕወሓት በበኩሉ፣ ከሕብረቱ ውጭ ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ በሁለቱ አካላት መካከል የሚካሔደው ድርድር በአፍሪካ ሕብረትና በሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ እንደሚመራ አስታውቋል፡፡

በምርት እጥረቱ ምክንያት ግለሰብ ሸማቾች ከ3 እስከ አምስት ብር የሚገዙትን አንድ ኪሎ ጨው እስከ 40 ብር አውጥተው ለመሸመት መገደዳቸውን ያስታወቁ ሲሆን ጨውን በግብአትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎችም የችግሩ ሰለባ እየሆኑ ነው ተብሏል፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/