ትረምፕ ምሬታቸውን እየገለፁ ነው

  • ቆንጂት ታዬ

Your browser doesn’t support HTML5

ፍሎሪዳ ማር-አ-ላጎ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ምርመራ ቢሮ የተፈተሸባቸው የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ "በፖለቲካ የተነሳሳ ጥቃት እየተፈፀመብኝ ነው" ብለዋል። የፌደራል ምርመራ ቢሮ ከትናንት በስተያ ሰኞ በቀድሞው ፕሬዚደንት መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ ያካሄደው የሥልጣን ዘመናቸውን አጠናቅቀው ከዋይት ሃውስ ሲወጡ ለብሄራዊው ቤተ መዛግብት ማስረከብ የነበረባቸውን የመንግሥት ሰነዶች ሳያስረክቡ ቀርተው እንደሆነ የሚያጣራ መሆኑ ተመልክቷል።