የኬንያ ምርጫ፣ ምሥራቅ አፍሪካና ኢትዮጵያ
Your browser doesn’t support HTML5
ኬንያዊያን ትናንት ሲሰጡ የዋሉት ድምፃቸው እየተቆጠረ ነው።
የኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ባለስልጣን(ኢጋድ) ያሠማራውን የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በመምራት እዚያው ኬንያ ይገኛሉ ።
ኢጋድ ዶ/ር ሙላቱን ታዛቢዎች ቡድኑ መሪ አድርጎ መሰየሙን ያስታወቀው ባለፈው ወር ሲሆን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርፕሮፌሰር መረራ ጉዲናም ከታዛቢዎች መካከል ናቸው።