የኢትዮጵያ የፍትኅ ሥርዓት፤ ለውጦችና ችግሮች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በተለይም በክልሎች የሚታየው የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ያለማክበርና ያለመፈፀም ችግር ህዝቡ በፍትኅ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዳይኖረው እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መአዛ አሸናፊና ምክትሎቻቸው ተናግረዋል ። ይሄም ሆኖ ግን የፍርድ ቤት ገለልተኛነትንና የዳኝነት ነፃነትን በተመለከተ ባለፉት ሦስት ዓመታት መሻሻል መስተዋሉን ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ አመልክተዋል።