ስንዴ ለማምረት የሚተጉ አርሶ አደሮች

Your browser doesn’t support HTML5

በኩታ ገጠም ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ስንዴ በማልማት ላይ የሚገኙ የምስራቅ አርሲ ዞን አርሶአደሮች እና የግብርናው ዘርፍ አመራሮች፣ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በስንዴ አቅርቦት ላይ የፈጠረው ክፍተት በቀጣዩ ዓመት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀረፍ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በምስራቅ አርሲ በሔክታር የሚገኘው የስንዴ ምርት በየዓመቱ በመጨመር ላይ መሆኑን የገለጹት የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገና መሐመድ፣ በዞኑ ዘንድሮ ከ21 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለማምረት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ ይህም በመንግስት የተያዘውን የኤክስፖርት እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው የገለጹት፡፡

ምንም እንኳን የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች ስጋት ቢኖርባቸውም፣ ኢትዮጵያ የቀጣዩን ዓመት የስንዴ ምርቷን ካለፈው ዓመት አንጻር ከ70 በመቶ በላይ ለማሳደግ አቅዳለች፡፡