ከተላከላቸው ገንዘብ ላይ 50 በመቶ የሚቆረጥባቸው የትግራይ ቤተሰቦች

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ትግራይ ክልልን ለቆ ከወጣ በኋላ ላለፉት 14 ወራት በክልሉ የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ በየትኛውም አካባቢ የሚኖር የቤተሰብ አባል ትግራይ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ ገንዘብ ለመላክ ቢፈልግ ከ20 እስከ 35 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅበት ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በኢንዲያና ክፍለ ግዛት የሴንት ሜሪ ኮሌጅ የቢዝነስ አስተዳደር ክፍለ ትምሕትር ኃላፊና መምህር ረዳት ፕሮፈሰሩ ዶ/ር አብራሪ ፍትዊ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የትግራይ ክልል ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ በትር ማሳረፉን ይናገራሉ።

በዚህ ዙሪያ ደረጀ ደስታ ከዚህ ከዋሽንግተን ሙሉጌታ አፅብሐ ከመቀሌ ያጠናቀሩት ዘገባ ነው።