አሜሪካ ኢትዮጵያ ላሉ ስደተኞች ትኩርት እየሰጠች ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ ለስደተኞች በቂ ድጋፍ እንዲደርስ ለማደረግ እየተጋች መሆኗን የሕዝብ፣ የስደተኞችና የፍልሰት ቢሮ ምክትል ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልዛቤጥ ካምፕቬል ገለፁ።

ጋምቤላ ክልልን ከትናንት ጀምረው የጎበኙት ምክትል ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ “ሙይይል” የሚባለውን ከመቶ ሺህ በላይ ስደተኞች የተጠለሉበትን ሠፈር ጎብኝተዋል።

ስደተኞቹም ያገኙት የነበረው የምግብ ድጋፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀነሱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል።