“ከ600 በላይ የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል” - የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት

Your browser doesn’t support HTML5

“ድንበር አልፈው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩ ከስድስት መቶ በላይ የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል” ሲል የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

በሶማሌ ክልል እየተካሄደ ባለው የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሃመድ “በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት ተፈርጇል” ካሉት አልሻባብ ጋር የሚደረገው ትግል እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ክልላቸው በዚህ ጥረቱ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ አመልክተዋል።

በዓለም ደረጃ የአደን ማስታወቂያ የወጣበትና ዩናይትድ ስቴትስ ላገኘው የአምስት ሚሊየን ብር ወሮታ እንደምትከፍል ቃል ገብታበት የነበረው ከአልሻባብ መሥራቾች አንዱ የሆነው አዛዥ ፉአድ ሞሃመድ ኻላፍ ወይም ፉአድ ሾንጎሌ መገደሉም ተነግሯል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/