የዓለም ጤና ድርጅት የአማካሪ ቡድን በዝንጀሮ ፈንጣጣ ጉዳይ ላይ ለሁለት ተከፍሏል

  • ቪኦኤ ዜና
ታሪኮ ቲመቲ በኒውዮርክ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ጸረ-ዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት ሲወስዱ ይታያሉ

ታሪኮ ቲመቲ በኒውዮርክ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ጸረ-ዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት ሲወስዱ ይታያሉ

የዓለም ጤና ድርጅት የአማካሪ ቡድን የዝንጀሮ ፈንጣጣ የዓለም እሳሳቢ የጤና ችግር ተብሎ በምን ደረጃ ይታወጅ በሚለው ላይ ለሁለት ተከፍሏል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአሳሳቢነት ደረጃውን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጡ ሲጠበቅ፣ ወረርሽኙን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ደረጃ ላይ ሊያስቀምጡት አንደሚችሉ ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሐሙስ ዕለት የተሰበሰበው የአማካሪ ቡድን ዋና ስራው ለዳይሬክተር ጄኔራሉ ምክር መለገስ ሲሆን፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የወረርስኙን አሳሳቢነት ደረጃ ማወጅን በተመለከተ ውሳኔ የመስጠት ሃላፊነት አለባቸው።

ይህ በአንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የጤና ባለስልጣናት በሃገሪቱ ሁለት ህጻናት የዝንጀሮ ፈንጣጣ እንደተገኘባቸው ትናንት አስታቀዋል።

አንደኛው ህፃን በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖር ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ በሀገሪቱ ነዋሪ ያልሆነና በዋሽንግተን ዲሲ የተመረመረ ህጻን አንደሆነ የሃገሪቱ የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከያ ማዕከል አስታውቋል።

በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት 2,800 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከዚህ ውስጥ ስምንቱ ሴቶች ናቸው።

በዓለም አስካሁን 14000 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ ለማወቅ ተችሏል።