የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ የሚሠሩ በጎ አድራጊ በዚምባቡዌ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በዚምባቡዌ ገጠራማ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለ አንድ ድርጅት ሴት ተማሪዎች የወር አበባቸው በሚመጣበት ጊዜ ከትምሕርት ቤት እንዳይቀሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በመሥራት ላይ ይገኛል። ጥረቱ የተጀመረው የአካባቢያቸው ሴቶች ልጆች በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እጦት ምክንያት ትምሕርታቸው እንዳይስተጓጎል ለማድረግ በተነሱ ቀድሞ መምህር በነበሩ አንዲት ሴት ነው። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታታሉ/