ዳባት ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ

Your browser doesn’t support HTML5

ዳባት ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ምግብን ጨምሮ መሰረታዊ አቅርቦቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ ህይወት እየገፉ መሆኑን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ እና በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ የተጠለሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ተናገሩ።

ተፈናቃዮቹ ይህንን የተናገሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን መጠለያ ጣቢያውን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ለእነሱና በአጠቃላይ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ልዩ ልዩ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን የገለፁት አምባሳደር ትሬሲ በበኩላቸው፤ የጉዟቸው ዓላማም ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን አስረድተዋል ።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/