ዳባት ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ

Your browser doesn’t support HTML5

ምግብን ጨምሮ መሰረታዊ አቅርቦቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ ህይወት እየገፉ መሆኑን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ እና በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ የተጠለሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ ይህንን የተናገሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን መጠለያ ጣቢያውን በጎበኙበት ወቅት ነው።